ኮንፊደንስ በመርፌ መልክ የሚሰጥ የእርግዝና መከላከያ ሲሆን፤ የተሰራውም በተፈጥሮ በሴቶች አካል ውስጥ ሚመረተውን ፕሮጀስትሮን አካላዊ ቅመም (ሆርሞን) ከሚመሳሰል ፕሮጀስቲን የተባለ በሳይንሳዊ መንገድ የተፈበረከ ንጥረ ነገር ነው፡፡
እያንዳንዱ የኮንፊደንስ ብልቃጥ ሜድሮክሲፕሮጀስትሮን አሲቴት 150ሚግ/ሚሌ ይዟል፡፡
ኮንፊደንስ በጡንቻ ውስጥ በመርፌ ከተሰጠ በኋላ ሆርሞኑ በደም ስሮች ውስጥ ቀስበቀስ ይሰራጫል፡፡
ኮንፊደንስ በየሶስት ወሩ የሚሰጥ የእርግዝና መከላከያ ነው፡፡
ኮንፊደንስ ጡት የሚያጠቡ እናቶችም ሊጠቀሙት የሚችሉ የእርግዝና መከላከያ ነው፡፡ ሆኖም ግን መሰጠት መጀመር ያለበት ከወለደች ስድስት ሳምንት እና ከዚያ በላይ ለሆናት የምታጠባ እናት ነው፡፡
በመርፌ የሚሰጥ
ኮንፊደንስ
አስተማማኝነቱ ምን ያህል ነው?
አስተማማኝነቱ እንደ ተጠቃሚዎቹ የአጠቃቀም ሁኔታ ይወሰናል:፡
ኮንፊደንስን ያለምንም ስህተት በትክክል ከሚጠቀሙ ሴቶች መካከል እርግዝና የመከሰት እድሉ 0.3% ብቻ ነው፡፡
ኮንፊደንስን ስትጠቀም የነበረች ሴት መርፌውን መውሰዷን በመተው ለማርገዝ ብትፈልግ እርግዝና ሳይከሰት እስከ አንድ ዓመት ድረስ ሊዘገይ ይችላል፡፡
ኮንፊደንስ ኤች.አይ.ቪን ጨምሮ ከማንኛውም ተላላፊ የአባላዘር በሽታዎች አይከላከልም፡፡
ጤና ነክ ጥቅሞች
ኮንፊደንስ እርግዝናን ከመከላከል በተጨማሪ የሚከተሉትን የጤና ችግሮች ለመከላከል ይረዳል ወይም ቀንሳል፡-
- የማህፀን ግድግዳና የእንቁልጢ ካንሰር
ካንሰር ያልሆነ የጡት ህመምን (Benign breast disease)
የማህፀን መደንደንን - የዳሌ ህመም እና መደበኛ ያልሆነ የደም መፍሰስን ይቀንሳል፡፡
በተጨማሪም - የማህፀን ቁስለትን እና የደም ማነስ ችግርን ሊከላከል ይችላል፡፡
ኮንፊደንስን መጠቀም የሚችሉት እነማን ናቸው
ኮንፊደንስ በአጠቃላይ ለሁሉም ሴቶች ተስማሚ እና ምቹ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ነው፡፡ ኮንፊደንስን መጠቀም የሚችሉ ሴቶች፡-
- ልጅ ያላቸው ወይም የሌላቸው
- ያገቡ ወይም ያላገቡ
- አፍላ ወጣቶች እና ከ40 አመት በላይ የሆናቸው ሴቶችን ጨምሮ በማንኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች
- በማንኛውም የዕድሜ ክልል ያሉ ሲጋራ የሚያጨሱ ሴቶች
- ፅንስ ያቋረጠች ወይም ያስወረዳት ሴት
- ጡት የሚያጠቡ እናቶች (ልጅ ከወለዱ ከስድስተኛው ሳምንት ጀምሮ)
ኮንፊደንስን መጠቀም የማይችሉት እነማን ናቸው
- ያረገዘች ወይም እንዳረገዘች የምትጠረጠር ሴት
- የጉበት ህመም ያለባት ሴት
- ጉበት መደበኛ ስራውን በትክክል ማከናወን የማይችልበት ሁኔታ ላይ ካለ
- የሠውነት እና የዓይን ቆዳ ቀለምን ወደ ቢጫ የሚቀይር የጉበት በሽታ ካለ ወይም ከነበረ
- መንስኤው ያልታወቀ የማህፀን መድማት ችግር ካለ
- የጡት ካንሠር ካለ
- የስኳር በሽታ ካለ
- ከፍተኛ የራስ ህመም ወይም ጭንቅላትን ከፍሎ የሚያም የራስ ምታት ካለ ወይም ከነበረ
- ኮንፊደንስ የተሰራበት ንጥረነገሮች እንደማይስማማት የተረጋገጠ ሴት
የጎንዮሽ ችግሮች
አንዳንድ ተጠቃዎች እነዚህን ሪፖርት አድርገዋል
- መጠነኛ የራስ ምታት
- ድብርት
- ማቅለሽለሽ (በአብዛኛው ከ2-3 ወራት ለሚሆን ጊዜ ከተጠቀሙ በኋላ ይህ ስሜት ይጠፋል)
- የጡት መደደር
- የክብደት መጨመር ወይም መቀነስ
- የስሜት መለዋወጥ (በጣም አልፎ አልፎ)
- ብጉር (ሊሻሻል ወይም ሊባባስ የሚችል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ግን ሊሻሻል የሚችል)