Skip links

ዲኬቲ ኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽያጭ ኮንፈረንስ አካሄደ፤ ከፍተኛ አፈጻጸም ያሳዩ ሰራተኞችንም የሽልማት እውቅና ሰጠ

በቅርቡ የተካሄደው የሽያጭ ሰራተኞች ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። ይህ ወሳኝ ክስተት የቤተሰብ ምጣኔን ከፊት ሆነው ለሚመሩ የሽያጭ ቡድን አባላትን በአዳዲስ ስልቶች፣ ለጠለቀ ስልጠናና ለጠንካራ ትብ ብር አንድነትን እንደሚያመጣ ተጠቅሷል።ኮንፈረንሱ የዲኬቲ ኢትዮጵያን ዋነኛ ዓላማ በድጋሚ ለማረጋገጥ አግዟል። ይኸውም ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን እና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኙ የወሊድ መቆጣጠሪያ ምርቶችን ለሁሉም የኢትዮጵያ ቤተሰብ ተደራሽ ማድረግ ነው።
በኮንፈረንሱ በመረጃ ላይ የተመሠረቱ ስልቶች፥በጋራ ችግር መፍታት፥ ምርጥ ተሞክሮዎችን መለዋወጥ።ምርቶችን በሚገባ ማወቅና በመረጃ የተደገፈ እውቀትን መለዋወጥ ጉዳዮችም ተዳሰዋል:: በመጨረሻም ከፍተኛ አፈጻጸም ላሳዩ ሰራተኞችንም የመስጋናና የሽልማት ፕሮግራም ተከናውኗል