Skip links

ዲኬቲ ኢትዮጵያ በ2018 ቱ የታላቁ የኢትዮጵያ የሴቶች 5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውጅር ላይ የይፋዊ መልዕክት ስፖንሰር በመሆን በኩራት ተሳትፏል።

ዲኬቲ ኢትዮጵያ በ2018 ቱ የታላቁ የኢትዮጵያ የሴቶች 5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውጅር ላይ የይፋዊ መልዕክት ስፖንሰር በመሆን በኩራት ተሳትፏል።
ለለጋሾቻችን፣ ለባልደረባዎቻችን እና ለደጋፊዎቻችን ፡ የእናንተ ኢንቨስትመንት ውጤቱ ይሄውላችሁ።
ይህ ዝግጅት ከሩጫ በላይ ነበር። በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ሴቶችን ጥንካሬ፣ ጤና እና ራስን የመቻል መብት ያቀነቀነ ታላቅ ንቅናቄ ነበር።
💡 አንዲት ሴት ህይወቷን የማቀድ አቅም ሲኖራት፣ በማይበገር በራስ መተማመን ወደፊት መጓዝ ትችላለች።
ዲኬቲ ኢትዮጵያ እንደ ስፖንሰርነቱ ይህንን መልዕክት በቀጥታ ወደ አደባባይ አውጥቶታል ፡ ሴቶች ባሉበት በመገኘት፣ ፅናታቸውን በማድነቅ እና ጤናቸው፣ ምርጫቸው እንዲሁም የወደፊት ህይወታቸው ትልቅ ዋጋ እንዳለው በማስታወስ።
🙏 ለለጋሾቻችን እና ለደጋፊዎቻችን፡ እናመሰግናለን። የእናንተ አጋርነት ከህክምና ተቋማት አልፈን ወደ ማህበረሰቡ እንድንደርስ አስችሎናል ፡ ማብቃት በተግባር በሚገለጽበት ቦታ ሁሉ ተገኝተናል። በጋራ በመሆን በእያንዳንዱ እርምጃ በራስ መተማመንን እያገነባን ነው።
በመላ ኑሪ ፡ በኮንፊደንስ ሩጪ!

#DKTEthiopia #GreatEthiopianWomenRun #WomensEmpowerment #FamilyPlanning #PublicHealth #Impact #DonorAppreciation #Partnerships #DKTInternational