Skip links

ዲኬቲ ኢትዮጵያ ለጤና ሚኒስቴር የ136 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

ዲኬቲ ኢትዮጵያ ለጤና ሚኒስቴር የ136 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
መጋቢት 08 ቀን 2017 የጤና ሚኒስቴር የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻልና ቅድመ መከላከል ላይ ሊሰራቸዉ በሚገቡ የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ህመምና ሞት ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ ይታወቃል።
ከዚህም መካከል አንዱ የሆነው የቤተሰብ ዕቅድ ፕሮግራሞችን ማስፋት በመሆኑ የቤተሰብ ዕቅድ/ ስነ ተዋልዶ ጤና ሀገራዊ ግብን ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረክት የሚገኘው ዲኬቲ ኢትዮጵያ ከጤና ሚኒኒስቴር ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በዛሬዉ እለትም ዲኬት ኢትዮጵያ ለጤና ሚኒስቴር በቤተሰብ እቅድ እና ስነ ተዋልዶ ዙሪያ ለሚሰራቸዉ ስራዎች 136 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ጤና ሚኒሰቴር ከዲኬቲ ኢትዮጵያ ያገኘውን የገንዘብና የግብዓት ድጋፍ ለአንድ አመት የሚቆይ እንደሆነ የገለፁት የጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ህፃናት አፍላ ወጣቶች ጤና መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ማርያማዊት አስፋው ናቸው።የእናቶች እና የህፃናት ሞትን ለመቀነስ እየተሰራ ያለውን ስራ ከፍ እንደሚያደርግ ገልጸዉ ድጋፉን የህክምና ግብዓት መሳሪያ ግዢ እንዲሁም የሰው ሀይል ሀብትን ለማሳደግ የሚውል እንደሆነም አመላክተዋል፡፡
ጤና ሚኒስትር ከዲኬቲ ኢትዮጰያ የተገኘውን ድጋፍ ተግባር ላይ ለማዋል በየክልሉ የቤተሰብ እቅድን ለመጠቀም ፍላጎቱ ኖሮ አቅርቦት ያልተዳረሰባቸውን ቦታዎች የመምረጥ ስራ በመስራት፤ የስነ-ተዋልዶ ህክምና መሳሪያዎችን ለመጠቀም የሚያስችል ብቃትን ለማሻሻል ስልጠናዎችን ለባለሙያዎች በመስጠት በቅርቡ ወደ ተግባር እንደሚገባ ጤና ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡