ዲኬቲ ኢትዮጵያ (DKT Ethiopia) የዘንድሮው የታላቁ የኢትዮጵያ የሴቶች ሩጫ ይፋዊ የመልዕክት አጋር (Official Message Partner) መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው!
“በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ”
ወደ መነሻ መስመሩ ይዘነው የመጣነው መሪ ቃል ከሩጫው በበለጠ እጅግ ጠንካራ መልዕክት ያዘለ ነው፦ በህይወት ውስጥ በራስ መተማመን የሚጀምረው በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ የማድረግ አቅም ሲኖር ነው።
ወደ መነሻ መስመሩ ይዘነው የመጣነው መሪ ቃል ከሩጫው በበለጠ እጅግ ጠንካራ መልዕክት ያዘለ ነው፦ በህይወት ውስጥ በራስ መተማመን የሚጀምረው በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ የማድረግ አቅም ሲኖር ነው።
በኢትዮጵያ የቤተሰብ እቅድ ፍላጎት ባልተሟላበትና አሁንም አሳሳቢ ፈተና ሆኖ ባለበት ሁኔታ፣ እንደነዚህ ያሉ አጋርነቶች እጅግ አስፈላጊ ናቸው። ንቁ እና ተነሳሽነት ካለው ከዚህ የሴቶች ማህበረሰብ ጎን በመቆም፣ ስፖርታዊ ኩነቱን ለጤና ግንዛቤ እና ለሴቶች አቅም ግንባታ ንቁ መድረክ እያደረግነው እንገኛለን።
የሩጫ ጫማዎቻችሁን ላሰረቻችሁ ሴቶች በሙሉ፦ የምትሮጡት በጥንካሬ ነው፣ የምትኖሩትም በእውቀት ነው።
ለተሳካ ሩጫ እንዲሁም ለጤናማ እና በራሷ ለምትተማመን ኢትዮጵያ!