Cart 0
የዲኬቲ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
Published on:
Published in:
ዜና
ዲኬቲ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ማይክል ኢቫንስ ሰኔ 3 ቀን 2013 ዓ.ም በተወለዱ በ61 አመታቸው በልብ ህመም ምክንያት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ዲኬቲን እና የቆመለትን አላማ ለማሳካት በጥልቅ ተነሳሽነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
በሰራተኞች ዘን ተወዳጅ የነበሩት ማይክል ኢቫንስ ዲኬቲ ኢትዮጵያን ወደ በርካታ አዳዲስ ሰትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች መርተውታል፡
ከሰኔ 2011 ዓ.ም ጀምሮ ዲኬቲ ኢትዮጵያን በዋና ዳይረክተርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ማይክል ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ዲኬቲ ቬትናምንም በተመሳሳይ ኃላፊነት ለስድሰት አመታት አገልግለዋል፡፡ ከ27 አመታት በላይ የአመራር ሰጪነት ልምድም አካብተዋል፡፡
እ.ኤ.አ በጁላይ 1 1960 አሜሪካ ካሊፎርኒያ ውስጥ የተወለዱት ማይክል ስቴቨን ኤቫንስ የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበሩ፡፡
ዲኬቲ ኢትዮጵያ በዋና ዳይሬክተሩ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፡፡
ውድ ማይክል
እንወድሃለን!
ልደትህንም አንተኑ በማሰብ በምትወደው መልኩ እናከብርልሃለን!
ነፍስህ በሰላም ትረፍ!