Skip links

የወንድ ኮንዶም

የወንድ ኮንዶም

የወንድ ኮንዶሞች ከስስ ላስቲክ የተሰሩ እና የወንዱን ብልት ወይም የሴቷን ብልት ውስጣዊ ክፍል የሚሸፍኑ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች ናቸው፡፡ ከእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች ውስጥ ኤች አይ ቪና የአባላዘር በሽታዎችን የሚከላከለው ኮንዶም ብቻ ነው፡፡ የአባላዛር በሽታዎች የተለያየ ዓይነት የመተላለፊያ መንገድ ያላቸው ሲሆኑ፤ በሠውነት ፈሳሽ ወይም በቀጥታ የቆዳ ንክኪ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ ኮንዶም እነዚህን የተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች የሚከላከልበት ደረጃ እንደየበሽታው መተላለፊያ መንገድ ይለያያል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ኮንዶም በቀጥታ የቆዳ ንክኪ ከሚተላለፉ የአባላዘር በሽታዎች ይልቅ በሠውነት ፈሳሽ የሚተላለፉ የአባላዛር በሽታዎችን ለመከላከል የበለጠ ውጤታማ ነው፡፡ በሠውነት ፈሳሽ የሚተላለፉ የአባላዛር በሽታዎች በባክቴሪያ አማካኝነት የሚከሰቱ እንደ ጨብጥ እና ቂጢኝ ያሉትን እንዲሁም በቫይረስ አማካኝነት የሚተላለፉ እንደ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ያሉትን ያጠቃልላል፡፡ ኮንዶም በቀጥታ የቆዳ ንክኪ ሊተላለፉ የሚችሉ የአባላዘር በሽታዎችን መተላለፍ ሊቀንስ የሚችለው በበሽታ የተጠቃው ቆዳ በኮንዶሙ እስከተሸፈነ ድረስ ብቻ ነው፡፡
የተለያየ ዓይነት ቃና ያላቸው የተለያዩ ኮንዶሞች አሉ፡፡ የኮንዶም ልዩ ቃና በራሱ በኮንዶሙ ወይም በያዘው ቅባት ውስጥ ሊኖር ይችላል፡፡ አንዳንዴም ቃና እንዲኖራቸው ተደርገው የተሰሩ ኮንዶሞች ከቃናቸው ጋር የሚመሳሰል ቀለም ይኖራቸዋል፡፡ ኮንዶምች በቅርፅ እና ልስላሴም የተለያዩ ዓይነት ተደርገው በመፈብረክ የሴቷን፣ የወንዱን ወይም የሁለቱንም እርካታ በሚጨምር መልኩ ይዘጋጃሉ፡

የወንድ ላቴክስ ኮንዶም
• የወንድ ላቴክስ ኮንዶም በቆመ የወንድ ብልት ላይ የሚጠለቅ ላቴክስ ከተሰኘ ስስ ላስቲክ የተሰራ መከላከያ ነው፡፡
• የወንዱ የዘር ፈሳሽ ወደ ሴቷ ማህፀን እንዳይገባ በማድረግ እርግዝናን ይከላከላል፡፡
• በዘር ፈሳሽ ውስጥ፣ በወንድ ብልት ላይ ወይም በሴት ብልት ውስጥ ያሉ ኢንፌክሽኖች ከወንዱ ወደ ሴቷ ወይም ከሴቷ ወደ ወንዱ እንዳይተላለፉ በማድረግ ኤች.አይ.ቪን ጨምሮ የአባላዘር በሽታዎችን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡
• የወንድ ኮንዶምን መጠቀም ባቆሙበት ቅፅበት ልጅ የማፍራት ተፈጥሯዊ ስጦታዎ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡

አስተማማኝነቱ ምን ያህል ነው?

አስተማማኝነቱ እንደ ተጠቃሚዎቹ አጠቃቀም ይወሰናል፡፡ኮንዶምን ሁል ጊዜና በአግባቡ መጠቀም ለውጤታማ መከላከል ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡

  • የወንድ ላቴክስ ኮንዶምን በዘላቂነት እና ሁል ጊዜም በትክክል ከተጠቀምነው 98% እርግዝናን ለመከላከል አስተማማኝ ነው፡፡
  • ኮንዶምን በእያንዳንዱ የግብረስጋ ግንኙነት ወቅት በትክክል ከተጠቀምነው ከ80% አስከ 95% ድረስ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ እንዳይተላለፍ ይከላከላል፡፡
  • ኮንዶሞች ለተለያዩ በግብረስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች የመጋለጥ እድልን ይቀንሳሉ፡፡
  • ኮንዶሞች በፈሳሽ የሚተላለፉ እንደ ጨብጥ ፣ ቂጥኝ እና ክላሚዲያ ያሉ የአባላዘር በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳሉ፡፡ ቁስለት ያለበት አካባቢ በኮንዶም የተሸፈነ ከሆነም  በቆዳ ለቆዳ ንክኪ የሚተላለፉ የአባላዘር በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳሉ፡፡

ጤና ነክ ጥቅሞች

የወንድ ኮንዶሞች እርግዝናን፣ ኤችአይቪን ጨምሮ የአባላዘር በሽታዎችን፣ ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ የተሰኙ የጉበት በሽታ አይነቶችን ለመከላከል ይጠቅማሉ፡፡

ስለ የወንድ ኮንዶም በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

የወንድ ኮንዶም ወንዶችን መካን ወይም ደካማ አያደረግም፡፡

የወንድ ኮምዶም የወንዶች ብልት እንዲቀንስ አያደርጉም፡፡

የወንድ ኮንዶም በሴቷ ብልት ውስጥ ሊጠፋ አይችልም፡፡

በአንድ ጊዜ ሁለትና ከዚያ በላይ ኮንዶሞችን ደራርቦ ማጥለቅ ተጨማሪ የመከላከል ብቃትን አያጎናፅፍም፡፡ ከዚህ ይልቅ በተደደራረቡት ኮንዶሞች መሀካል በሚፈጠር ፍትጊያ በግንኙነት ጊዜ ኮንዶሞቹ እንዲወልቁ ወይም እንዲቀደዱ ሊያደርግ ይችላል፡፡

በትክክል፡፡ በርካታ ባለትዳሮች የወንድ ኮንዶምን እንደ እርግዝና መከላከያ ዘዴ ይጠቀማሉ፡፡

የጎንዮሽ ችግሮች

የወንድ ኮንዶም በመጠቀም የሚከስት የጎንዮሽ ችግር የለም፡፡  ነገር ግን እጅግ በጣም አልፎ አልፎ ለላቴክስ አለርጂ በሆኑ ሰዎች ላይ የአለርጂ ስሜቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡