Skip links

ለምለም

ለምለም

ለምለም በተቅማጥ በሽታ ሊከሰት የሚችለውን የሠውነት ፈሳሽ እጥረት የሚተካ ህይወት አድን ንጥረነገር ነው፡፡ ለምለም በዋንኛነት ህፃናት በተቅማጥ በሽታ አማካኝነት ለሚከሰት ከፍተኛ የሠውነት ፈሻስ እጥረት እንዳይጋለጡና ለህልፈት እንዳይዳረጉ በመከላከልና በማከም ህይወታቸውን ይታደጋል፡፡ እያንዳንዱ የለምለም እሽግ በውስጡ ሶስት ከረጢት ለምለም ህይወት አድን ንጥረነገር (ኦ.አር.ኤስ) ይዟል፡፡ ተቅማጡ በሶስት ቀን ጊዜ ውስጥ ካልተሻለ ወይም ከተባባሰ ወይም ተቅማጡ ደም የተቀላቀለበት ከሆነ ወይም ከተቅማጡ በተጨማሪ ሌላ የህመም ስሜት ካጋጠመ ህፃኑን ወደጤና ተቋም በመውሰድ ተገቢውን ህክምና እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ለምለም ፕላስ

ለምለም ፕላስ በተቅማጥ በሽታ ሊከሰት የሚችለውን የሠውነት ፈሳሽ እጥረት የሚተካ ህይወት አድን ንጥረነገር (ኦ.አር.ኤስ) እና ዚንክ እንክብልን የያዘ ማከሚያ እሽግ ነው፡፡ እያንዳንዱ የለምለም ፕላስ እሽግ በውስጡ ሁለት ለምለም ህይወት አድን ንጥረነገር (ኦ.አር.ኤስ) እና 10 ፍሬ በቀላሉ የሚሟሟ ባለ 20ሚ.ግ የዚንክ ንጥረነገር እንክብሎችን ይዟል፡፡ ለምለም ኦ.አር.ኤስ ህፃናት በተቅማጥ በሽታ አማካኝነት ለሚከሰት ከፍተኛ የሠውነት ፈሻስ እጥረት እንዳይጋለጡና ለህልፈት እንዳይዳረጉ በመከላከልና በማከም ህይወታቸውን ይታደጋል፡፡ ዚንክ ንጥረነገር ተቅማጥ እንዲቀንስ፣ ለብዙ ጊዜ እንዳይቆይ እና ህመሙ እንዳይባባስ ይረዳል፡፡ በተጨማሪም ዚንክ ንጥረነገር ከ2-3 ወራት ለሚሆን ጊዜ ሌላ ዙር ተቅማጥ ሳይዝ ለመቆየት የሚያስችል በሽታን የመቋቋም አቅም ይሰጣል፣ የህፃናትን የምግብ ፍላጎት ያሻሽላል እንዲሁም በሽታን የመቋቋም አቅማቸውን ያጎለብታል፡፡