Skip links

ኮንዶሞችና ቅባት

የወንድ ኮንዶም

የወንድ ኮንዶሞች ከስስ ላስቲክ የተሰሩ እና የወንዱን ብልት ወይም የሴቷን ብልት ውስጣዊ ክፍል የሚሸፍኑ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች ናቸው፡፡ ከእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች ውስጥ ኤች አይ ቪና የአባላዘር በሽታዎችን የሚከላከለው ኮንዶም ብቻ ነው፡፡ የአባላዛር በሽታዎች የተለያየ ዓይነት የመተላለፊያ መንገድ ያላቸው ሲሆኑ፤ በሠውነት ፈሳሽ ወይም በቀጥታ የቆዳ ንክኪ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ ኮንዶም እነዚህን የተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች የሚከላከልበት ደረጃ እንደየበሽታው መተላለፊያ መንገድ ይለያያል፡፡

ተጨማሪ

ስሙዝ ሙቭ

ስሙዝ ሙቭ ለስላሳ፣ ዘይትነት የሌለው፣ የማያጣብቅ፣ ሽታ እና ቀለም አልባ ማለስለሻ ቅባት ሲሆን

  • በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት ተጨማሪ ማለስለሻ ቅባት ለሚያስፈልጋቸው ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፤
  • ከላቴክስ ኮንዶሞች ጋር መጠቀም የሚቻል ሲሆን፤ የግብረስጋ ግንኙነት በሚደረግበት ወቅት ሊፈጠር የሚችልን ድርቀት በማስወግድ የወንድ ላቴክስ ኮንዶምን ከመቀደድ ይታደጋል፤
  • ለግብረስጋ ግንኙነት ዝግጁ በሆነ የወንድ ብልት ወይም በሴት ብልት ላይ ወይንም በኮንዶም የላይኛው ክፍል ላይ ያለስጋት ሊደረግ ይችላል፤
  • ዘይትነት የሌለው ቅባት ስለሆነ በቀላሉ በመታጠብ ይፀዳል፤ ቆዳ ላይ የሚቀር ነገር የለውም፡፡
  • ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት ወይንም በጤና ላይ ሊያስከትለው የሚችል ችግር የለም፡፡
  • እያንዳንዱ ስሙዝ ሙቭ በውስጡ 5 ሚሊ ሊትር ማለስለሻ ቅባት ይዟል፡፡
ተጨማሪ