Cart 0
የወንድ ኮንዶሞች ከስስ ላስቲክ የተሰሩ እና የወንዱን ብልት ወይም የሴቷን ብልት ውስጣዊ ክፍል የሚሸፍኑ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች ናቸው፡፡ ከእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች ውስጥ ኤች አይ ቪና የአባላዘር በሽታዎችን የሚከላከለው ኮንዶም ብቻ ነው፡፡ የአባላዛር በሽታዎች የተለያየ ዓይነት የመተላለፊያ መንገድ ያላቸው ሲሆኑ፤ በሠውነት ፈሳሽ ወይም በቀጥታ የቆዳ ንክኪ ሊተላለፉ ይችላሉ፡፡ ኮንዶም እነዚህን የተለያዩ የአባላዘር በሽታዎች የሚከላከልበት ደረጃ እንደየበሽታው መተላለፊያ መንገድ ይለያያል፡፡


