Skip links
በአፍ የሚወሰዱ እንክብሎች

ስታይል

ስታይል በአፍ የሚወሰድ ባለጥምር አካላዊ ቅመም የእርግዝና መከላከያ እንክብል ሲሆን፤ የተሰራውም በተፈጥሮ በሴቶች አካል ውስጥ የሚመረቱትን ኤስትሮጅን እና ፕሮጀስትሮን አካላዊ ቅሞች (ሆርሞኖች) ከሚመሳሰሉ በጣም ዝቅተኛ መጠን ካላቸው ኤስትሮጅን እና ፕሮጀስቲን የተባሉ በሳይንሳዊ መንገድ የተፈበረኩ ንጥረ ነገሮች ነው፡፡ ስታይል ባለ ሶስት ደረጃ (ማለትም የሴቷን የወር አበባ ዑደት ተክትሎ የተለያየ መጠን ያላቸው ኢስትሮጅን እና ፕሮጀስቲን ሆሮሞኖች ይዘት ያላቸው እንክብሎችን የያዘ) እና ባለ ሆርሞን በአፍ የሚወሰድ የዕርግዝና መከላከያ እንክብል ነው፡፡
እያንዳንዱ የስታይል እሽግ ባለ 21 ፍሬ ሲሆን፤ ይዘታቸው ሌቮኖርጀስትሪል 0.05 ሚ.ግ + ኢትናይልእስትራዲዮል 0.03 ሚ.ግ የሆነ 6ፍሬ ቡኒ ፣ ይዘታቸው ሌቮኖርጀስትሪል 0.075 ሚ.ግ + ኢትናይልእስትራዲዮል 0.04 ሚ.ግ የሆነ 5ፍሬ ነጭ እና ይዘታቸው ሌቮኖርጀስትሪል 0.125 ሚ.ግ + ኢትናይልእስትራዲዮል 0.03 ሚ.ግ የሆነ 10ፍሬ ቢጫ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎችን ይይዛል፡፡

አስተማማኝነቱ ምን ያህል ነው?

አስተማማኝነቱ እንደ ተጠቃሚዎቹ የአጠቃቀም ሁኔታ ይወሰናል:፡ ሴቷ የስታይል እንክብል የያዘውን አዲስ እሽግ ሶስት ቀናት እና ከዚያ በላይ ዘግይታ ከጀመረች ወይንም የእንክብል እሽጉን በምትጀምርበት ወይም በምትጨርስበት ቀናት አካባቢ ለሶስት ቀናት እና ከዚያም በላይ የእርግዝና መከላከያ እንክብሉን ሳትወስድ ከቀረች እርግዝና የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

የስታይል እንክብል በትክክል ከተወሰደ እና አወሳሰዱ ላይ ችግር ከሌለ ደግሞ እንክብሉን ከሚጠቀሙ 1000 ሴቶች ውስጥ በመጀመሪያው ዓመት ውስጥ እርግዝና ሊከሰት የሚችለው በ3ቱ ሴቶች ላይ ብቻ ነው፡፡

የስታይል እንክብል ስትጠቀም የነበረች ሴት እንክብሉን መውሰዷን በመተው ለማርገዝ ብትፈልግ ወዲያውኑ ማርገዝ ትችላለች፡፡

ስታይል ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ጨምሮ ከማንኛውም ተላላፊ የአባላዘር በሽታዎች አይከላከልም፡፡

ስታይል ከሴቶች የተፈጥሮአዊ ወር አበባ ዑደት ጋር እንዲመሳሰል ተደርጎ የተለያየ የአካላዊ ቅመም ይዘት ካላቸው እንክብሎች የተዘጋጀ በመሆኑ እርግዝናን ከመከላከል በተጨማሪ የወር አበባ መዛባትን ለማስተካከል መጠቀም ይቻላል፡፡

ጤና ነክ ጥቅሞች

ስታይል እርግዝናን ከመከላከል በተጨማሪ የሚከተሉትን የጤና ችግሮች ለመከላከል ይረዳል፡-

  • የማህፀን ግድግዳ ካንሰር
  • የእንቁልጢ ካንሰር
  • የማህፀን ቁስለት
  • ከወር አበባ መዛባት እና መብዛት ጋር የተያያዙ የደም ማነስ ችግሮችን

የሚከተሉትን ደግም ይቀንሳል፡-

  • በወር አበባ ጊዜ የሚከሰተውን የሆድ ቁርጠት
    በዉጻት ጊዜ የሚፈጠር የህመም ስሜት
    በሰዉነት ወይም በፊት ላይ የጸጉር መብዛትን ይቀንሳል

ስታይልን መጠቀም የሚችሉት እነማን ናቸው

ስታይል በአጠቃላይ ለሁሉም ሴቶች ተስማሚ እና ምቹ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ነው፡፡ ቾይስን መጠቀም የሚችሉሴቶች፡-

  • ልጅ ያላቸው ወይም የሌላቸው
  • ያገቡ ወይም ያላገቡ
  • አፍላ ወጣቶች እና ከ 40 ዓመት በላይ የሆናቸው ሴቶችን ጨምሮ በማንኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶች
  • ፅንስ ያቋረጠች ወይም ያስወረዳት ሴት
  • የደም ማነስ ያለባቸው ወይም በፊት የነበረባቸው ሴቶች
  • የፀረ ኤች.አይ.ቪ መድሀኒት ቢወስዱም ባይወስዱም ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ሴቶች ቾይስንበአስተማማኝነት መጠቀም ይችላሉ፡፡
  • ሴቶች ስታይልን ፡

ምንም የማህፀን በር እና  የማህፀን አካባቢ እንዲሁም ምንም ዓይነት የላቦራቶሪ ምርመራ ሳያደርጉ ለእርግዝናመከላከያነት መጠቀም መጀመር ይችላሉ፡፡

ስታይልን መጠቀም የማይችሉት እነማን ናቸው

  • ያረገዘች ወይም እንዳረገዘች የምትጠረጠር ሴት
  • ባለፈው 3 ወራት ጊዜ ውስጥ የወለደች እናት
  • ከወለደች 6 ወራት ወይም ከዚያ በታች የሆናት የምታጠባ እናት
  • በሳንባ ውስጥ የደም መርጋት ካለ ወይም ከነበረ
  • ከዚህ በፊት በጭንቅላት እና የደም ስሮች ላይ የደረሰ አደጋ ከነበረ
  • የልብ እና የልብ ቧንቧ ህመም ካለ ወይም ከነበረ
  • ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ያለባቸው ሴቶች
  • ከደም ዑደት ጋር የተቆራኘ የስኳር በሽታ ካለ
  • ከነርቭ ጋር የተያያዘ የራስ ም ታት ካለ
  • የጡት ካንሰር ካለ
  • የጉበት ካንሰር ካለ
  • የጉበት ህመም ችግር ካለ
  • በቀን ከ15 ሲጋራዎች በላይ የሚያጨሱ እና ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ የሆነ ሴቶች
  • እንክብሉ የተሰራበት ንጥረነገሮች እንደማይስማማት የተረጋገጠ ሴት

የጎንዮሽ ችግሮች

አንዳንድ ተጠቃዎች እነዚህን ሪፖርት አድርገዋል

  • መጠነኛ የራስ ምታት
  • ድብርት
  • ማቅለሽለሽ (በአብዛኛው ከ2-3 ወራት ለሚሆን ጊዜ ከተጠቀሙ በኋላ ይህ ስሜት ይጠፋል)
  • የጡት መደደር
  • የክብደት መጨመር ወይም መቀነስ
  • የስሜት መለዋወጥ (በጣም አልፎ አልፎ)
  • ብጉር (ሊሻሻል ወይም ሊባባስ የሚችል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ግን ሊሻሻል የሚችል)

ስለ ቾይስ ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ሴቷ በዚያ ቀን የግብረ ስጋ ግንኙነት ብታደርግም ባታደርግም እንክብሉን በየቀኑ መውሰድ አለባት፡፡

አንድ ሴት ስታይል መጠቀም ካቆመች በኋላ ወዲያውኑ ወደ ተፈጥሯዊ ልጅ የማፍራት ችሎታዋ ትመለሳለች፡፡ ስታይል ሴቶች መካን እንዲሆኑ አያደርግም፡፡

ስታይል በእርግዝና ላይ ምንም የሚያስከትለው ችግር የለም፡፡ ሴቶች አካለ ጎዶሎ ወይም መንታ ልጅ እንዲወልዱም ምክንያት አይሆንም፡፡

ስታይል በሴቶች የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎት ላይ ምንም ዓይነት ለውጥ አያስከትልም፡፡

እያንዳንዱ የስታይል  እንክብል በየቀኑ ስለሚሟሟ በጨጓራ ወይም በሰውነት ውስጥ አይከማችም፡፡