መላ-ዋን በአፍ የሚወሰድ የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ እንክብል ነው፡፡ ይህ የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ዘዴ በማስገደድ ወይም ባልተጠበቀ ሁኔታ በተከናወነ ጥንቃቄ በጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት ሳቢያ እንዲሁም የታወቀ ወይም የሚጠረጠር የሌሎች የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች አለመስራት ሲኖር ሊከሰት የሚችለውን ያልተፈለገ እርግዝና የግብረስጋ ግንኙነት በተፈጠረ በ72 ሰዓታት ጊዜ ውስጥ ለመከላከል የሚጠቅም ነው፡፡
መላ-ዋን ባለነጠላ አካላዊ ቅመም የያዘ ሲሆን የተሰራውም በሴቶች አካል ውስጥ በተፈጥሮ ከሚመረተው ፕሮጀስትሮን አካላዊ ቅመም (ሆርሞን) ጋር ከሚመሳሰል ፕሮጀስቲን ከሚባል ንጥረነገር ነው፡፡ እያንዳንዱ የፋሲል-ዋን እሽግ በውስጡ አንድ ባለ 1.5 ሚ.ግ ሌቮኖርጀስትሪል እንክብል ይዟል፡፡