Skip links

መላ ዋን

የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ

መላ ዋን

መላ-ዋን በአፍ የሚወሰድ የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ እንክብል ነው፡፡ ይህ የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ዘዴ በማስገደድ ወይም ባልተጠበቀ ሁኔታ በተከናወነ ጥንቃቄ በጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት ሳቢያ እንዲሁም የታወቀ ወይም የሚጠረጠር የሌሎች የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች አለመስራት ሲኖር ሊከሰት የሚችለውን ያልተፈለገ እርግዝና የግብረስጋ ግንኙነት በተፈጠረ በ72 ሰዓታት ጊዜ ውስጥ ለመከላከል የሚጠቅም ነው፡፡

መላ-ዋን ባለነጠላ አካላዊ ቅመም የያዘ ሲሆን የተሰራውም በሴቶች አካል ውስጥ በተፈጥሮ ከሚመረተው ፕሮጀስትሮን አካላዊ ቅመም (ሆርሞን) ጋር ከሚመሳሰል ፕሮጀስቲን ከሚባል ንጥረነገር ነው፡፡ እያንዳንዱ የፋሲል-ዋን እሽግ በውስጡ አንድ ባለ 1.5 ሚ.ግ ሌቮኖርጀስትሪል እንክብል ይዟል፡፡

አስተማማኝነቱ ምን ያህል ነው?

እርግዝናን የመከላከል አስተማማኝነቱ እንደ ተጠቃሚዎች አጠቃቀም ይለያያል፡፡ እንክብሉ ጥንቃቄ የጎደለዉ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በተፈጸመ በ72 ሰዓታት ጊዜ ውስጥ መወሰድ አለበት፡፡ ጊዜዉ እየጨመረ ሲሄድ የመከላከል አቅሙ እየቀነሰ ስለሚሄድ የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን ወዲያውኑ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡
መላ-ዋን በማስገደድ ወይም ባልተጠበቀ ሁኔታ በተከናወነ ጥንቃቄ በጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት ሳቢያ ሊከሰት የሚችለውን እርግዝና ለመከላከል የሚወሰድ እንክብል እንጂ በዘላቂነት የሚወሰድ መደበኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ አለመሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
መላ-ዋን ኤች.አይ.ቪን ጨምሮ ከማንኛውም ተላላፊ የአባላዘር በሽታዎች አይከላከልም፡፡

መላዋንን መጠቀም የሚችሉት እነማን ናቸው?

እርግዝና ላይ እስካልሆነች ድረስ ማንኛዋም ሴት ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴን መጠቀም ትችላለች፡፡

መላዋንን መጠቀም የማይችሉት እነማን ናቸው

ያረገዘች ወይም እንዳረገዘች የምትጠረጠር ሴት

  • እንክብሉ የተሰራበት ዋና ንጥረነገር (ሌቮኖርጀስትሪል) እንደማይስማማት የተረጋገጠ ሴት
  • መንስኤው ያልታወቀ ወይም ምንነቱ በምርመራ ያልተረጋገጠ የደም መፍሰስ ያላት ሴት
  • ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የጉበት ህመም ያለባት ሴት
  • ጥንቃቄ የጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት ካደረገች 72 ሰዓታት ያለፋት ሴት

የጎንዮሽ ችግሮች

  • የወርአበባ መዛባት ለምሳሌ
  • እንክብሉ በተወሰደ ጥቂት ቀናት ውስጥ መጠነኛ የሆነ የደም መፍሰስ ሊከሰት ይችላል፡፡
  • የወር አበባ ከሚጠበቅበት ጊዜ ቀድሞ ወይም ዘግይቶ ሊመጣ ይችላል፡
  • ማቅለሽለሽ
  • ማስመለስ
  • ከእምብርት በታች የሆድ ቁርጠት
  • ድብርት / የመጫጫን ስሜት
  • የድካም ስሜት / የሠውነት መዛል
  • የራስ ምታት
  • የጡት መደደር