Skip links

ፖስትፒል

የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ

ፖስትፒል

ፖስትፒል በአፍ የሚወሰድ ባለሆርሞን የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ እንክብል ነው፡፡ ይህ የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ዘዴ በማስገደድ ወይም ባልተጠበቀ ሁኔታ በተከናወነ ጥንቃቄ በጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት ሳቢያ እንዲሁም የታወቀ ወይም የሚጠረጠር የሌሎች የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች አለመስራት ሲኖር ሊከሰት የሚችለውን ያልተፈለገ እርግዝና የግብረስጋ ግንኙነት በተፈጠረ በ72 ሰዓታት ጊዜ ውስጥ ለመከላከል የሚጠቅም ነው፡፡

ፖስትፒል ባለነጠላ አካላዊ ቅመም የያዘ ሲሆን የተሰራውም በሴቶች አካል ውስጥ በተፈጥሮ ከሚመረተው ፕሮጀስትሮን አካላዊ ቅመም (ሆርሞን) ጋር ከሚመሳሰል ፕሮጀስቲን ከሚባል ንጥረነገር ነው፡፡ እያንዳንዱ የፖስትፒል እሽግ በውስጡ ሁለት ባለ 0.75 ሚ.ግ ሌቮኖርጀስትሪል እንክብሎች ይዟል፡፡

አስተማማኝነቱ ምን ያህል ነው?

እርግዝናን የመከላከል አስተማማኝነቱ እንደ ተጠቃሚዎች አጠቃቀም ይወሰናል፡፡ እንክብሉ ጥንቃቄ የጎደለዉ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በተፈጸመ በ72 ሰዓታት ጊዜ ውስጥ መወሰድ አለበት፡፡ ጊዜዉ እየጨመረ ሲሄድ የመከላከል አቅሙ እየቀነሰ ስለሚሄድ የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን ወዲያውኑ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡
ፖስትፒል በማስገደድ ወይም ባልተጠበቀ ሁኔታ በተከናወነ ጥንቃቄ በጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት ሳቢያ ሊከሰት የሚችለውን እርግዝና ለመከላከል የሚወሰድ እንክብል እንጂ በዘላቂነት የሚወሰድ መደበኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ አይደለም፡፡
ፖስትፒል ኤች.አይ.ቪን ጨምሮ ከማንኛውም ተላላፊ የአባላዘር በሽታዎች አይከላከልም፡፡

የጎንዮሽ ችግሮች

  • የወርአበባ መዛባት
  • እንክብሉ በተወሰደ በከ1-2 ቀናት ውስጥ መጠነኛ የሆነ የደም መፍሰስ ሊከሰት ይችላል፡፡
  • የወር አበባ ከሚጠበቅበት ጊዜ ቀድሞ ወይም ዘግይቶ ሊመጣ ይችላል፡፡
  • ማቅለሽለሽ
  • ማስመለስ
  • ከእምብርት በታች የሆድ ቁርጠት
  • የድካም ስሜት / የሠውነት መዛል
  • የድካም ስሜት / የሠውነት መዛል
  • የራስ ምታት
  • የጡት መደደር