Skip links
በማህፀን ውስጥ የሚቀመጥ 

ሎንግአክት (ሉፕ)

ሎንግአክት (ኮፐር-ቲ 380ኤ) በማህፀን ውስጥ የሚቀመጥ የእርግዝና መከላከያ ትንሽ፣ ተጣጣፊ እና ቀጭን የመዳብ ጥቅል በላዩ ከያዘ ፕላስቲክ የተሰራ ነው፡፡ ሎንግአክት የእንግሊዝኛ ፊደል “T”ን የሚመስል ቅርፅ ያለው ሲሆን፤ በታችኛው ጫፉ ላይ የሚገኝ ባለቀለም ተንጠልጣይ ክር መሰል ጭራ በማህፀን ውስጥ ከተቀመጠ በኋላ ቦታውን ሳይለቅ በተገቢው ሁኔታ መቀመጡን ለመፈተሽና ለማረጋገጥ ይጠቅማል፡፡ ሎንግአክት እስከ 12 ዓመታት እርግዝናን ይከላከላል፡፡ ሎንግአክት ለረጅም ጊዜ እርግዝና መከላከያነት ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ እንደ ድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዘዴም ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

አስተማማኝነቱ ምን ያህል ነው?

ሎንግአክት በማህፀን ውስጥ የሚቀመጥ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ በዓለም ላይ ካሉ ዘመናዊ የእርግዝና መከላከያዎች ውስጥ እጅግ በጣም አስተማማኝ ውጤት ያለው ዘዴ ነው፡፡

በማህፀን የሚቀመጥ የእርግዝና መከላከያ ከሚጠቀሙ 100 ሴቶች መካከል በመጀመሪያው ዓመት እርግዝና ሊከሰት የሚችለው በ 0.7ቱ ላይ ብቻ ነው፡፡

ጤና ነክ ጥቅሞች

ሎንግአክት ወይም ዩ-ኬር እርግዝናን ከመከላከል በተጨማሪ የሚከተሉትን የጤና ችግሮች

ለመከላከል ይረዳል፡-

የማህፀን ግድግዳ ካንሰር እና
የማህፀን በር ካንሰ

ሎንግአክትን መጠቀም የሚችሉት እነማን ናቸው

ሎንግአክት በመውለድ እድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ሴቶች ሁሉ ለማለት በሚያስችል ደረጃ ተስማሚና ምቹ የእርግዝና መከላከያ ነው፡፡

 • በማንኛውም የእድሜ ደረጃ ላይ የሚገኙ
 • ልጅ ያላቸው ወይም የሌላቸው
 • ያገቡ ወይም ያላገቡ

ሎንግአክትን መጠቀም የማይችሉት እነማን ናቸው

 • ያረገዘች ወይም እንዳረገዘች የምትጠረጠር ሴት
 • መንስኤው ያልታወቀ የደም መፍሰስ ካለ
 • ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሴቷ ለአባላዘር በሽታ ተጋልጣ ከነበረ
 • ሴቷ ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና አጋጥሟት የሚያውቅ ከነበረ ወይም
 • ከማህፀን ውጪ ሊፈጠር ለሚችል እርግዝና ተጋላጭ ከሆነች
 • በተፈጥሮ ወይም በሌላ ምክንያት የማህፀን ቅርጽና አቀማመጥ ላይ ችግር ካለ
 • የማህጸን ቁስለት ካለ

የጎንዮሽ ችግሮች

አንዳንድ ተጠቃሚዎች እነዚህን ሪፖርት አድርገዋል

 • በወር አበባ ላይ የሚከሰቱ ለውጦች ለምሳሌ፡- የወር አበባ መዛባት (በተለይ በመጀመሪያዎቹ 3 እስከ 6 ወራት) ማለትም
 • በወር አበባ ጊዜ ብዙ ደም መፍሰስ እና ወር አበባ የሚፈስባቸው ቀናት መርዘም
 • በወር ውስጥ በማንኛውም ቀን የሚከሰት የደም መፍሰስ
 • በወር አበባ ጊዜ ሊሰማ የሚችል የሆድ ቁርጠት እና የህመም ስሜት መባባስ

ስለ ሎንግአክት በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ሎንግአክት ከማህፀን ውስጥ ከወጣ በኋላ ሴቷ ብታረግዝ ውርጃ የመከሰት እድልን አይጨምርም

ሎንግአክት ሴቶች መካን እንዲሆኑ አያደርግም

ሎንግአክት ለካንሰር በሽታ አያጋልጥም?

ሎንግአክት ከማህፀን ውጪ ተንቀሳቅሶ ወደ ልብና ጭንቅላት መሰል ሌሎች የሴቷ  የሰውነት ክፍሎች አይዘዋወርም ፡፡ ሴቷ በየጊዜው በትክክለኛ ቦታው ላይ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባታል፡፡

ሎንግአክት በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የህመም ስሜት አይፈጥርም፤ ምቾትም አይቀንስም፡፡ ምንም እንኳን በተለምዶ የሚወራ ቢሆንም ሎንግአክት በማህፀን ውስጥ ከሚቀመጥበት ቦታ አንፃር በግብረስጋ ግንኙነት ወቅት የወንዱን ብልት ሊነካው አይችልም፡፡

በሰለጠነ የጤና ባለሙያ ወደሚሰጡ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች  ገጽ ውስጥ እየገቡ ነው ፡፡

የዚህ ገጽ ይዘቶች ለመረጃ ዓላማዎች ብቻ ናቸው ፡፡ መረጃዎቹ ማንኛውንም የሕክምና ሁኔታ ለመመርመር

እና / ወይም ለማከም የታሰቡ አይደሉም፤ እናም ለሙያዊ የሕክምና ምክር ምትክ ሆነው መተርጎም የለባቸውም።

በዚህ ገጽ ላይ የሚገኙትን ማናቸውንም  የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች ለመጠቀም ከወሰኑ

እባክዎን ወደ ሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች ይሂዱ፡፡