Skip links

ስለ-እኛ

ስለ እኛ

ዲኬቲ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ1990 የተመሰረተ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ማህበራዊ ግብይትን በመከተል የቤተሰብ እቅድን ለማስፋፋት፣ ኤችአይቪን ለመከላከል፣ እንዲሁም የእናቶችና ህፃናት ጤናን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ምርቶችን በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያ የቤተሰብ እቅድ አገለግሎት ዘዴዎችን ተደራሽነትና አጠቃቀም በማስፋት፣ የኤችአይቪ ኤድስ ስርጭትን በመከላከል እንዲሁም የእናቶችና ህፃናት ጤናን በማሻሸል ረገድ አስደናቂ ውጤት አስመዝግባለች፡፡ የእርግዝና መከላከያ ስርጭት መጠን እ.ኤ.አ በ1990 ከነበረበት 3% በ2019 ወደ 41% አድጓል፡፡ የኤች አይ ቪ ስርጭት ደግሞ በ1996 ከነበረበት 3.2% አሁን ወደ 0.8% ወርዷል (የአለም ባንክ)፡፡

እነዚህ ውጤቶች ቢኖሩም አሁንም 23.7% የሚሆኑ የኢትዮጵያ ሴቶች የቤተሰብ እቅድ ዘዴ ፍላጎት አልተሟላም፡፡ ኤችአይቪ በአንዳንድ ቁልፍ የማህበረሰብ ክፍሎች እና አካባቢዎች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል፡፡ የእናቶችና ህፃናት ሞት ከአብዛኞቹ የአለም ሀገራት አንፃር ከፍተኛ ነው፡፡

ዲኬቲ ኢትዮጵያ በ1990 በእንድ ምርት ብቻ ነበር ስራውን የጀመረው -በህይወት ትረስት ኮንዶም፡፡ አሁን ላይ ዲኬቲ ሁለት የኮንዶም መለያዎችና አይነቶችን ፣ በአፍ የሚወሰዱ፣ በመርፌ የሚወሰዱ፣ በክንድ ቆዳ ስር የሚቀመጡ፣ በማህፀን የሚቀመጡ እና የድንገተኛ የእርግዝና መከላከያ ዜዴዎችን እንዲሁም ሌሎች በርካታ የእናቶችና ህፃናት ጤና ምርቶችን ያቀርባል፡፡

ተልዕኮ

ዲኬቲ ለጥንዶች የገቢ አቅምን ያገናዘቡ እና ተመራጭ የሆኑ የቤተሰብ ዕቅድ ዘዴዎችን፣ ደኅንነታቸው የተረጋገጠ ለጽንስ ማቋረጥ አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶችና ቴክኖሎጂዎችን እንዲሁም ለኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከል የሚጠቅሙ አማራጮችን በማኅበራዊ ግብይት አገልግሎት አማካኝነት ማቅረብ ነው፡፡

ራዕይ

ልጆች ተፈልገው የሚወለዱበት ፣ ጾታዊ ግንኙነት የሚከበርበት እና ሰዎች በነፃነት የሚወስኑበት ዓለም መፍጠር

ወጪን መተካት

ዲኬቲ ለአንድ የጥንዶች አመታዊ የእርግዝና መከላከያ (ሲዋይፒ) የሚያወጣው ወጪ ከ4-5 ዶላር ገደማ ይደርሳል፡፡ ይህም ዲኬቲን በአፍሪካ ለሲዋይፒ ዝቅተኛውን ወጪ ከሚያወጡት ተርታ ያሰልፈዋል (ጉትማቸር 2019)፡፡፡ ከሽያጭ የሚገኘው ገቢ ከማይተነበዩ የፖለቲካ እና የለጋሾች ቀዳሚ አጀንዳዎች መቀያየር ጋር ተያይዞ ሊፈጠር የሚችለውን ጫና ተቋቁሞ እንዲሰራ ይረዳዋል፡፡

ደረጃ

ዲኬቲ ኢትዮጵያ ውስጥ ለግሉ ዘርፍ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን በማቅርብ ትልቁ ድርጅት ነው፡፡ በአጠቃላይ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች አቅርቦት ረገድ ደግሞ ከመንግስት ቀጥሎ ሁለተኛው ነው፡፡ በ2023 ዲኬቲ 4.27 ሚሊዮን ለጥንዶች የሚያስፈልጉ አመታዊ የእርግዝና መከላከያዎች (ሲዋይፒ) በማሰራጨት በአፍሪካ ሁለተኛው የማህበራዊ ግብይት ፕሮግራም መሆን ችሏል፡፡

ዲኬቲ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሰራ ሲሆን ሰባት ያልተማከሉ አካባቢያዊ ቢሮዎች፣13 መጋዘኖች እና አነስተኛ ምርት ማስቀመጫዎች አሉት፡፡

ለጥንዶች የሚያስፈልጉ አመታዊ የእርግዝና መከላከያዎች (ሲዋይፒ)

Aለጥንዶች የሚያስፈልግ አመታዊ የእርግዝና መከላከያ ማለት ለአንድ አመት የሚያስፈልጉ የተለያዩ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት ዘዴዎችን በማንፀሪያነት ለመለካት ጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡ 1 ሲዋይፒ ከ

  • 100 የወንድ ኮንዶሞች
  • 100 የሴት ኮንዶሞች
  • 14 በአፍ የሚወሰዱ የእርግዝና መከላከያ እንክብል እሽጎች
  • 16 የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ እንክብል እሽጎች
  • 4 በመርፌ የሚሰጡ የእርግዝና መከላከያዎች
  • 0.23 በማህፀን የሚቀመጡ የእርግዝና መከላከያዎች
  • 0.33 በክንድ ቆዳ ስር የሚቀመጡ የእርግዝና መከላከያዎች ጋር እኩል ነው፡፡

ንግድ ተኮር መያድ

ዲኬቲ የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮችን ለመፍታት እንደ ንግድ ተቋም የሚሰራ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡ በአስርት አመታት ሂደት ውስጥ በደንበኞቹ ዘንድ ተዓማኒነትን ያተረፉና ተደራሽ የሆኑ ብራንዶችን ገንብቷል፡፡ ሰዎች የከፈሉበትን ነገር የመጠቀም እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ በማመንም ምርቶችን በነፃ ከማደል ይልቅ በሽያጭ ያከፋፍላል፡፡

ዲኬቲ ከሚያከፋፍላቸው ምርቶች አንዳንዶቹ በከፍተኛ ደረጃ ድጎማ የሚደረግላቸው ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ በመጡበት ዋጋ እና መጠነኛ ትርፍ ታክሎባቸው የሚሸጡ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ አብዛኞቹ የስነተዋልዶ ጤና ምርቶች በመንግስት ዘርፍ የሚቀርቡ ሲሆን ዲኬቲ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ እንዳለው መንገድ የግሉን ዘርፍ ይመርጣል፡፡

ዲኬቲ የሚለው ስያሜ

ዲኬቲ  ህንድ ውስጥ ረዳት የቤተሰብ እቅድ ኮሚሽነር ሆኖ ላገለገለው ዲ.ኬ (ዲፕ) ቲያጂ ክብር የተሰየመ ነው፡፡ ቲያጂ በመቶ ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ህንዳውያን ዘመናዊ የቤተሰብ እቅድ ዘዴዎችን ያስተዋወቀ ሰፊ የተግባቦትና የባህሪ ለውጥ ፕሮግራምን የፈጠረ ሰው ነው፡፡ በዋናነትም በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ህንዳውያን በቤተሰብ እቅድ ላይ ግንዛቤና እውቀት እንዲኖራቸው ያስቻሉ ሰፋፊ የተግባቦት ፕሮግራሞችን በመፍጠርና በማሰራጨት ይታወቃል፡፡ ቲያጂ ስራውን የጀመረው በህንድ ገጠራማ አካባቢዎች ዘመናዊ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች እምብዛም በማይተወቁበት በ1966 ነበር፡፡ ቲያጂ ህንድን ቀላል እና ማራኪ በሆኑ የቤተሰብ እቅድ መልዕክቶች እና ዲዛይኖች (አሁን በበርካታ ሀገራት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለውን ቀይ ትራያንግል ጨምሮ) በማጥለቅለቅ፣  ዘመናትን ያስቆጠሩ የተግባቦት መሰናክሎችን በማለፍ የህዝቡን የእርግዝና መከላከያ ግንዛቤ በማሳደግ ስኬታማ ተግባራትን አከናውኗል፡፡

ኡታር ፕራዲሽ ውስጥ ካለችው መንደሩ ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳለው ህንዳዊ  በመንግስት የቤተሰብ እቅድ ግቦችና በገጠራማ አካባቢዎች በሚኖሩ ህንዳውያን ባህላዊ ፍላጎቶች መካከል ያስተዋለውን ከፍተት በማጥበብ የቲያጂ ስራ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ ገና በ41 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ቢለይም ቲያጂ ለሀገሩ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት የማስፋፋት ጥረቶች ጉልህ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

ስለለጋሾቻችን

ዲኬቲ ኢትዮጵያ በርካታ ለጋሾች ለሚያደርጉለት ድጋፍ ምስገናውን ያቀርባል፡፡