Skip links

የሴት ኮንዶም

የሴት ኮንዶም

የሴት ኮንዶም በሴቷ ብልት ውስጥ የሚደረግ ከስስ ፕላስቲክ የተሰራ መከላከያ ነው፡፡ ከስስ፣ ለስላሳና ባለቅባት ፕላስቲክ የተሰራ በመሆኑ በግንኙነት ጊዜ ከወንድ ኮንዶም አንፃር የተሻለ ተፈጠሯዊ ስሜትን ይሰጣል፡፡ በውጭም በውስጥም በኩል ሁለት ተጣጣፊ ቀለበቶች ያሉት ሲሆን የውስጠኛው ቀለበት ለሴቷ ተጨማሪ ደስታን የሚፈጥር ነው፡፡

አስተማማኝነቱ ምን ያህል ነው?

አስተማማኝነቱ እንደ አጠቃቀሙ ይወሰናል፡፡ የሴት ኮንዶምን ሁል ጊዜና በአግባቡ ባለመጠቀም ለአልታቀደ እርግዝና እና ለአባላዘር በሽታዎች የመጋለጥ እድል እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡

ሁል ጊዜና በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋለ የሴት ኮንዶም እርግዝና እና የአባላዘር በሽታዎችን ለመከላከል 95 በመቶ ውጤታማ ነው፡፡

ጤና ነክ ጥቅሞች

የሴት ኮንዶም ያልታቀደ እርግዝና እና ኤች አይ ቪን ጨምሮ የአባላዘር በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳል፡፡

ስለሴት ኮንዶም ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

የሴት ኮንዶም በሴቷ ማህፀን ውስጥ ሊጠፋ አይችልም

የሴት ኮንዶም ለአጠቃቀም ከባድ አይደለም፡፡ ልክ እንደ ወንድ ኮንዶም ሁሉ ተጠቃሚዎች በኮንዶሙ ማሸጊያ ላይ ያሉትን የአጠቃቀም መመሪያዎች በመከትል የሴት ኮንዶምን  በትክክል መጠቀም ይችላሉ፡፡

በትክክል! የሴት ኮንዶሞች  በትዳር ውስጥ ላሉ ጥንዶችም እንደ እርግዝና መከላከያ ምርጫ ያገለግላሉ፡፡