ዲኬቲ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ስትራቴጂካዊ የፋርማሲ ማነቃቂያዎችን በማድረግ የስነ፡ተዋልዶ ጤና ምርቶች አቅርቦትን አስፋፋ
ዲኬቲ ኢትዮጵያ የስነ፡ተዋልዶ ጤናን ለማዳረስ በሚያደርገው ጉዞ ላይ ትልቅ ምዕራፍ መድረሱን በኩራት ይገልጻል። ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋንን ለማረጋገጥ ካለን ቀጣይነት ያለው ቁርጠኝነት አካል በመሆን፣ በአዲስ አበባ በተለያዩ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች የፋርማሲ ማነቃቂያ ፕሮግራምን በስኬት አስጀምረናል።
ይህ ማነቃቂያ ጥራታቸውን የጠበቁ እና ተመጣጣኝ የጤና ምርቶች ከአጋር ፋርማሲዎቻችን በኩል ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ መሆናቸውን ያረጋግጣል። ብማነቃቂያ ፕሮግራም ውስጥ የተሳተፉት ፋርማሲዎች የሚከተሉት ናቸው፦አባድር ፋርማሲ ፣ ሳፋሪ ፋርማሲ ፣ መዝሙረ ዳዊት ፋርማሲ ፣ ዶንዶር ፋርማሲ ፣ እሰገነት ፋርማሲ ፣ ፒዩር ሜድ ፋርማሲ ፣ አማሪ ፋርማሲ ይገኙበታል
ይህ የስራ ማስፋፊያ የጤና መፍትሄዎችን ለአዲስ አበባ ህዝብ ይበልጥ ለማቅረብ ያለንን የማይናወጥ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ደንበኛ የሚገባውን እንክብካቤ እና ክብር እንዲያገኝ ያረጋግጣል።