Skip links

ፒፒአይዩዲ

ድህረ ወሊድ በማህፀን ውስጥ የሚቀመጥ የእርግዝና መከላከያ (ፒፒአይዩዲ) በጤና ተቋማት ውስጥ የወለዱ ሴቶች እንዲጠቀሙት የሚበረታታ የረጅም ጊዜ የእርግዝና መከላከያ ነው፡፡ ፒፒአይዩዲ ሴቷ በወለደች እና እንግዴ ልጁ በወጣ በ48 ሰዓታት ውስጥ ሊደረግ የሚችል ሲሆን መውለድ በፈለገችበት ሰዓት በባለሙያ መልሳ በማስወጣት ማርገዝ ትችላለች፡፡

ሆርሞን አልባ የእርግዝና መከላከያ ነው
2 በመቶ እርግዝናን የመከላከል ብቃት አለው
ሴቷ ካስወጣቸው በኋላ የማርገዝ ችሎታዋ ወዲያውኑ ይመለሳል

አስተማማኝነቱ ምን ያህል ነው?

ፒፒአይዩዲ በማህፀን ውስጥ የሚቀመጥ የእርግዝና መከላከያ ዘዴ በዓለም ላይ ካሉ ዘመናዊ የእርግዝና መከላከያዎች ውስጥ እጅግ በጣም አስተማማኝ ውጤት ያለው ዘዴ ነው፡፡99.2 በመቶ እርግዝናን የመከላከል ብቃት አለው፡፡

ጤና ነክ ጥቅሞች

ሎንግአክት ወይም ዩ-ኬር እርግዝናን ከመከላከል በተጨማሪ የሚከተሉትን የጤና ችግሮች

ለመከላከል ይረዳል፡-

  • የማህፀን ግድግዳ ካንሰር እና
  • የማህፀን በር ካንሰር

ፒፒአይዩዲን መጠቀም የሚችሉት እነማን ናቸው

ፒፒአይዩዲ በመውለድ እድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ሴቶች ሁሉ ለማለት በሚያስችል ደረጃ ተስማሚና ምቹ የእርግዝና መከላከያ ነው፡፡

  • በማንኛውም የእድሜ ደረጃ ላይ የሚገኙ
  • ልጅ ያላቸው ወይም የሌላቸው
  • ያገቡ ወይም ያላገቡ

ፒፒአይዩዲን መጠቀም የማይችሉት እነማን ናቸው

  • ያረገዘች ወይም እንዳረገዘች የምትጠረጠር ሴት
  • መንስኤው ያልታወቀ የደም መፍሰስ ካለ
  • ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሴቷ ለአባላዘር በሽታ ተጋልጣ ከነበረ
  • ሴቷ ከማህፀን ውጪ የሚፈጠር እርግዝና አጋጥሟት የሚያውቅ ከነበረ ወይም
  • ከማህፀን ውጪ ሊፈጠር ለሚችል እርግዝና ተጋላጭ ከሆነች
  • በተፈጥሮ ወይም በሌላ ምክንያት የማህፀን ቅርጽና አቀማመጥ ላይ ችግር ካለ
  • የማህጸን ቁስለት ካለ
  • ሴቷ መዳብ አለርጂ ካለባት

የጎንዮሽ ችግሮች

አንዳንድ ተጠቃዎች እነዚህን ሪፖርት አድርገዋል

  • በወር አበባ ላይ የሚከሰቱ ለውጦች ለምሳሌ፡- የወር አበባ መዛባት (በተለይ በመጀመሪያዎቹ 3 እስከ 6 ወራት) ማለትም
  • በወር አበባ ጊዜ ብዙ ደም መፍሰስ እና ወር አበባ የሚፈስባቸው ቀናት መርዘም
  • በወር ውስጥ በማንኛውም ቀን የሚከሰት የደም መፍሰስ
  • በወር አበባ ጊዜ ሊሰማ የሚችል የሆድ ቁርጠት እና የህመም ስሜት መባባስ

በሰለጠነ የጤና ባለሙያ ወደሚሰጡ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች  ገጽ ውስጥ እየገቡ ነው ፡፡

የዚህ ገጽ ይዘቶች ለመረጃ ዓላማዎች ብቻ ናቸው ፡፡ መረጃዎቹ ማንኛውንም የሕክምና ሁኔታ ለመመርመር

እና / ወይም ለማከም የታሰቡ አይደሉም፤ እናም ለሙያዊ የሕክምና ምክር ምትክ ሆነው መተርጎም የለባቸውም።

በዚህ ገጽ ላይ የሚገኙትን ማናቸውንም  የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች ለመጠቀም ከወሰኑ

እባክዎን ወደ ሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች ይሂዱ፡፡